ዘላቂ የልማት ግቦችን ማሳካት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረው የተ.መ.ድ የፖለቲካ ፎረም እየተካሄደ ነው

ሐምሌ 5፣2009

የሀገራት ተወካዮች እየተሳተፉበት ያለው በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፖለቲከ ፎረም ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ አተኩሯል። 

አጀንዳ 2030ን ለመተግበር ሁሉም በአንድነት መነሳት እንዳለበት ፎረሙን የከፈቱት የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ፍሬድሪክ ሙሲዋ ማካሙሬ ሻቫ ተናግረዋል።

የዘንድሮ ስብሰባ አለም ላይ ድህነትን ለመቀነስና እድገትን ለማበረታታት በአውሮፓውያኑ 2015 ከፀደቀው አዲሱ የልማት አጀንዳ ወዲህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው አሁን እየተካሄደ ያለው

በስብሰባው ላይ የሚነሱት ውይይቶች ድህነት እና ረሃብን መቀነስ፣ጤናማ ኑሮ ማረጋገጥ፣ ጾታዊ እኩልነትን ማረጋገጥ፣ ጠንካራ መሰረተ ልማቶችን መገንባት፣ ተባባሪዎችን መፍጠር እና ውቅያኖሶችን መንከባከብ እንዲሁም ዘላቂ ጥቅም ላይ ማዋል በሚሉ ጉዳዮች ላይ እንደሚያተኩሩ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም ፎረሙ በ44 አገራት ውስጥ የልማት መርሃግብሮችን ለመድረስ በሚያጋጥሙ ችግሮችና ልዩ ክፍተቶች ላይም ይመክራል ተብሏል።

ከሐምሌ 4 እስከ 12 በኒውዮረክ እየተካሄ ባለው የፖለቲካ ፎረም ላይ ከ70 በላይ ሚንስትሮች ተሳታፊ መሆናቸው ታውቋል፡፡

ምንጭ- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት