የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁስ ውጋጆችን በስርዓት ለማስወገድ ጥምረት ተፈጠረ

ሐምሌ 06፤2009

የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁስ ውጋጆችን በተገቢው መንገድ ለመሰብሰብ እና ለማስወገድ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስር የታቀፉት ኤጄንሲዎች በጋራ መስራት መጀመራቸውን አለም አቀፉ የቴሌኮሚኒኬሽን ማህበር አስታወቀ፡፡

የኤሌክትሮኒክስ ቴክኖሎጂዎች እየተሻሻሉ በመጡ ቁጥር የአገልግሎት ጊዜያቸውም እያጠረ እንደሚመጣና ለጥገናም ሆነ መልሶ አገልግሎት ላይ ለማዋልም አዳጋች እንደሆኑ ተነግሯል፡፡

የኤሌክትሮኒክስ ውጋጆች አወጋገድ ስርዓትን በተገቢ መንገድ ለመምራት ደግሞ የአለም ሀገራትና ባለድርሻ አካላት አለም አቀፍ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች አወጋገድ ስታስቲክስ አጋርነት ፈጥረው እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ ተጠቁሟል፡፡

ሀገራት በትክክለኛ የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶች አወጋገድ መረጃ  እንዲኖራቸው፤ የአቅም ግንባታ እንዲሰጣቸው፤ በአወጋገድ ስርዓቱ እና ክትትሉ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ እንዲሰጣቸው ያግዛል ነው የተባለው፡፡

አብዛኞቹ ውጋጅ የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶች ተመዝግበው አይያዙም እንዲሁም በትክክለኛው የመልሶ ጥቅም ላይ የማዋል ሂደት ውስጥ አያልፉም ነው የተባለው፡፡

እ.ኤ.አ በ2017 እስከ 50 ሚሊዮን ቶን የሚደርሱ ጥቅም የማይሰጡ የኤሌክትሮኒክስ ውጋጅ ቁሳቁሶች እንደሚወገዱ የመንግስታቱ ድርጅት የአካባቢ ፕሮግራም አመልክቷል፡፡

ምንጭ፦ሽንዋ