የዓለም ሙቀት መጨመሩን ሰባት መቶ በሚጠጉ ተፈጥሯዊ ዘዴዎች ማረጋገጣቸውን ተመራማሪች ገለፁ

ሐምሌ 06፣2009

የዓለም ሙቀት ከመቼውም ጊዜ መጨመሩን ሰባት መቶ በሚጠጉ ተፈጥሯዊ ዘዴዎች ማረጋገጣቸውን ተመራማሪች ገለፁ፡፡

የአለምን ሙቀት ከመቸውም ጊዜ በላቀ  መጨመሩን ለመረጋገጥ 692 የተለያዩ ተፈጥሯዊ መንገዶችን መጠቀማቸውን በጥናቱ የተካተቱት አንድ መቶ ተመራማሪዎች  በግኝታቸው ይፋ አድርገዋል፡፡

በዚህም በሁሉም አህጉራት ከጥንት ጀምሮ እስከአሁን ድረስ ያለውን ለማነፅር አስችሎናል ብለዋል፡፡

ተፈጥሯዊ ዘዴዎች ብለው ተመራማሪዎቹ ከተጠቀሙባቸው መንገዶች መካከል ታሪካዊ  መረጃዎች፣የዛፍ ቅሬቶች፣ለረጅም ጊዜ ሳይፈርሱ የቆዩ የበረዶ ቅሬት፣ሀይቆችና  የባህር ውስጥ ደለልና አለቶች፣የማዕድናት ክምችትና ተፅፈው የተቀመጡ ማስረጃዎች ከብዙ በጥቂቱ ጥቅም ላይ ማላቸውን ተመራማሪቹ ተናግረዋል፡፡

በግኝቱ መሰረት የአለማችን ሙቀት ከዛሬ 2 ሺህ አመት ወዲህ እስካሁን ድረስ እየጨመረ መምጣቱንና በተለይም ከ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ  ወዲህ ክፉኛ ማሻቀቡ ተመልከቷል፡፡

ለዚህም በዋነኛ ምክንያትነት የተቀመጠው በኃይል አማራጭነት ጥቅም ላይ በዋላው የቅሬተ አካል የኃይል አጠቃቀም ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቀውን የካርቦንዳይ ኦክሳይድ  መጠን ክፉኛ እንዲጨምር አድርጎታል፡፡ ይህም ከፍተኛ ሙቀት እንዲጨምር ምክንያት ሆኗል ይላል አዲሱ ግኝት፡፡

ተመራማሪዎች ጥቅም ላይ ባዋሉት ተፈጥሯዊ የሙቀትን መጨመር መለካት ዘዴ የሁለት ሺህ ዓመት መረጃዎችን በሰባቱም ክፍለ ዓለማት በ648 ቦታዎች ላይ መሰረት ያረገ ጥናት አካሂደዋል፡፡

ተፈጥሯዊ ዘዴን በመጠቀም የአለም ሙቀት መጨመርን ይፋ ያደረጉት ግኝት የአለም ሙቀት መጨመር የፈጠራ ወሬ ነው ብለው ለሚከራከሩ ወገኖች ሁነኛ ማስረጃ ይሆናል ተብሏል፡፡

በተለይም በአሁኑ ግዜ በአለም አቀፍ ደረጃ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም ወደ ስምምነት የተመጣበትን ከቶኪዮ ፖሮቶኮል እስከ ኮፐን ሀገን እንዲያም ሲል እስከ ፓሪሱ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት ድረስ የአለምን ሙቀት መጠን ከ2 ድግሪ ሴንቲግሬድ ለማውረድ የተደረሰውን አቋም ለመናድ ለሚነቀሳቀሱት ወገኖች ሞጋች ማስረጃ ሆኖ ቀርቧል፡፡

ምንጭ ፡‑ ኢንዲፔንደንት