ጊኒ ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚና ግብርና ዘርፍ ተሞክሮ መውሰድ እንደምትፈልግ ገለጸች

ሐምሌ 07፣2009

ጊኒ ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚና ግብርና ዘርፍ ተሞክሮ መውሰድ እንደምትፈልግ ገለፀች፡፡

በኢትዮጵያ የጊኒ አምባሳደር ሲዲብ ፋቱማታ ካባ እንዳሉት ኢትዮጵያ በአለም ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገቡ ካሉ 10 ሀገራት መካከል አንዷ ነች፡፡

ጊኒ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት ግንኙነት በየጊዜው እያደገ መሆኑን የተናገሩት አምባሳደሩ፤ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ የተለያዮ ዘርፎች በተለይም ከኢኮኖሚ እድገትና ግብርና ተሞክሮ ለመቀመር ፍላጎት እንዳላት ገልፀዋል፡፡  

የጊኒ ፕሬዝዳንት አልፋ ኮንዴ በስራቸው የሚገኙ የፋይናንስ፣ የኢንዱስትሪና የአለም አቀፍ ትብብር ሚንስትሮች ከኢትዮጵያ ልማት ተሞክሮ እንዲወስዱ ማሳሰባቸውን አምባሳደሯ አመልክተዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጊኒ ነጋዴዎች የውጭ ጉዟቸው የተቀላጠፈ እንዲሆን ምቹ ሁኔታ መፍጠሩንም ተናግረዋል፡፡

በአብዛኛው በማዕድንና በግብርና ምርቶች ላይ የተመሰረተው የጊኒ ኢኮኖሚ፤ ‹‹ቦክሳይ›› በተባለ የአለት ምርት በማምረት በአለም ሁለተኛ ደረጃን ይዟል። አገሪቱ በአልማዝና በወርቅ ማዕድናትም የበለፀገች ናት፡፡ 

ምንጭ፦ሽንዋ