የመከላከያ ሚንስትር ሲርጅ ፈጌሳ ከኳታሩ አሚር ጋር በዶሃ መከሩ

ሐምሌ 08፣2009

የኢፌዲሪ መከላከያ ሚንስትር ሲርጅ ፈጌሳ  ከኳታሩ  አሚር ጋር  በሁለትዮሽ አገራዊ ጉዳች ላይ በዶሃ መከሩ፡፡

በኳታር የስራ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት የመከላከያ ሚንስትሩ ኣቶ ሲራጅ ፈጌሳ ከሚመሩት ልዑካን ቡድን  ጋር በመሆን በኢትዮጵያና  በኳታር የሁለትሽ የጋራ ጥቅሞች ላይ ከአገሪቱ አሚር ሼኽ ተሚም ቢን ሃማድ አልሳኒ ጋር መክረዋል፡፡

በውይይቱም ሁለቱ አገራት በተለያዩ ዘርፎች የሚያካሂዱትን ትብብር  ለማጎልበት መስማማታቸውን  ገልፍ ታይምስ ዘግቧል፡፡

የመከላከያ ሚንስትሩ ሲራጅ ፈጌሳ ከኳታሩ አቻቸው ጋር  ቀደም ብሎ መምከራቸውም ተዘግቧል፡፡

ኳታር ከገልፍ አገራት ጋር በገባችው  ፖለቲካዊ መቃቃር ኢትዮጵያ  ከኩዌት ጋር በመሆን ለመሸምገል ፍላጎት እንዳላት መግለጿ ይታወሳል፡፡