በ3 መቶ ሚሊዮን ብር የተገነባው የሃላባ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ስራ ጀመረ

ሐምሌ 08፣2009

በ3 መቶ ሚሊዮን ብር ከ114 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ተገንብቶ የተጠናቀቀው  የሀላባ የንፅህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት በይፋ ስራ ጀመረ፡፡

በሀላባ ልዩ ወረዳ ጥርስን ለብልሽት በሚዳርግ የፍሎራይድ  ንጥረ ነገር የተሞላ በመሆኑ የልዩ ወረዳዋን ውሃ ፍላጎት ለማሟላት ከስልጤ ዞን ሁልባረግ ወረዳ ላይ የተገነባው የውሃ ፕሮጀክት ነው ተጠናቆ በዛሬው ዕለት ለምረቃ  የበቃው፡፡

በሁለቱ ወረዳዎች መካከል የ114 ኪሎ ሜትር ርቀት ቢኖርም ከ3መቶ ሚሊዮን ብር በላይ በፈጀ ወጪ የልዩ ወረዳውን የውሃ ችግር የሚቀርፍ ፕሮጀክት በሁለት አመት ገደማ ተገንብቶ እውን ሆኗል፡፡

በስልጤ ዞን ከምትገኘው የሁልባረግ ወረዳ ዕውም የሆነው ፕሮጀክቱ  በሁለቱ ወረዳዎች ለሚገኙ 21 ቀበሌዎች የሚኖር 110ሺ ህዝብን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል በስነ  ስርዓቱ ላይ፡፡

የውሃ ፕሮጀክቱ ወጪ የተሸፈነው በክልሉ  መንግስት ነው፡፡

የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደሴ ዳልኬ በስ ስርዓቱ ላይ እንዳሉት የክልሉ ህዝብ የሚያነሳቸውን የመልካም አስደተዳደርና የልማት ጥያቄዎች የክልሉ መንግስት ደረጃ በደረጃ እፈታ ይሄዳል፡፡

የሀላባልዩ ወረዳን የውሃ ችግር ይቀርፋል የተበላው የውሃ ፕሮጀክትም መንግስት የገጠር ንፅህ መጠጥ ውሃን ለማዳረስ ያየዘውን ጥረት የሚያሳይ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

የውሃ ፕሮጀክቱ መመረቅ 33 በመቶ የነበረውን ልዩ ወረዳዋን የውሃ ሽፋን 51 በመቶ እንደሚያደርሰውም በስነ ስርዓቱ ላይ ተመልክቷል፡፡

ከስልጤ ዞን ተስቦ የመጣው የሀላባ ንፅህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የህዝብ ለህዝብ ትስስርን የሚያጠናክር የልማት ውጤት በመሆኑ አስደሳች ነው ሲሉ የሀላባ ልዩወረዳ ነዋዎች ለኢቢሲ ተናግረዋል፡፡

የውሃ ፕሮጀክቱ ለሚቀጥሉት 45 አመታት በሙሉ አቅሙ አገልግሎት እንዲሰጥ ታስቦ ነው የተገነባው፡፡

ሪፖርተር ፡‑ ሀብታሙ ድረስ