ሲኦል ከፒዮንጊያንግ ጋር ወታደራዊ ውይይት ማድረግ እንደምትፈልግ ገለፀች

ሐምሌ 10፣2009

በኮሪያ ልሳነ ምድር የነገሰውን ውጥረት ለማብረድ  ሲኦል ከፒዮንጋንግ ጋር ወታደራዊ ውይይት ማድረግ እንደምትፈልግ ገለፀች፡፡

ሰሜን ኮሪያ የረጅም ርቀት ተወንጫፊ ሚሳኤል ከፈፀመች በኋላ በኮሪያ ልሳነ ምድር የከረረ ውጥረት ነግሶ ቆይቷል፡፡

ደቡብ ኮሪያ በአፀፋ መልክ ከአሜሪካ ጋር በመሆን ወታደራዊ ልምምድ እስከ  ማድረግም  ደርሳ  ነበር፡፡

በዚህም በሀለቱ አገራት መካከል ተካሮ የነበረውን ውጥረት ለማብረድ  ደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ወይይት  ማድረግ እንደምትፈልግ አስታውቃለች፡፡

የደቡብ ኮሪያ ከፍተኛ ባለስልጣን እንደተናገሩት በሁለቱ አገራት ድንበር አቅራቢያ ያለውን ውጥረት ለማብረድ ንግግሩ መፍትሄ ይሆናል፡፡

አዲሱ የደቡብ ኮሪያ ፕሬዝዳንት ሙን ጃኢም ቢሆን ከሰሜን ኮሪያ ጋር ያለውን ቅርርብ ለማጠናከር ፍላጎት ያላቸው  መሪ መሆናቸውን ሲገልፁ ተሰምቷል፡፡

ደቡብ ኮሪያ የንግግር ጥሪውን ለጎረቤቷ  ብታቀርብም  ከሰሜን ኮሪያ ግን ምንም የተሰጠ ምላሽ የለም፡፡

ምንጭ ፡‑ ቢቢሲ