በአለማችን የመጀመሪያው ተንሳፋፊ የንፋስ ሃይል ማመንጫ ስራ ጀመረ

ሃምሌ 18፤2009

በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነው በባህር ላይ ተንሳፋፊ የንፋስ ሃይል ማመንጫ ተርባይን በስኮትላንድ ተግባራዊ መደረጉ ተገለጸ፡፡

ይህ አስደናቂ የቴክኖሎጂ ፈጠራ በባህር ላይ የሚነፍሰውን ከፍተኛ ንፋስ በቀላሉ በመጠቀም የኤሌክትሪክ ሃይልን ማመንጨት እንደሚቻል ነው ቢቢሲ የዘገበው፡፡

ቴክኖሎጂው ሃይዊንድ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን በመጀመሪያ ሙከራው ለ20 ሺህ መኖሪያ ቤቶች የኤሌክትሪክ ሃይል ያቀርባል ነው የተባለው፡፡

ተንሳፋፊ የንፋስ ሃይል ማመጫዎቹ በባህር ሞገድ ጉዳት እንዳያደርስባቸውም ከባህር ወለል ጋር በገመድ ታስረው እንዲቀመጡ መደረጉ ተበግሯል፡፡

ቴክኖሎጂው ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት ላለፉት ስድስት አመታት የሙከራ ተግባር ሲከናወን እንደነበር ተገልጿል፡፡

ምንጭ፡ ቢቢሲ