የኬንያ ልጃገረዶች የሴቶች ግርዛትን መከላከል የሚያስችል የሞባይል መተግበሪያ ፈጠሩ

ሃምሌ 18፤2009

5 የኬንያ ልጃገረዶች የሴቶች ግርዛትን መከላከል የሚያስችል የሞባይል መተግበሪያ/አፕሊኬሽን/ መፍጠራቸውን ገለፁ፡፡

እድሜያቸው ከ15 እስከ 17 የሚደርሱት እነዚህ ልጃገረዶች የፈጠራ ውጤታቸውን የሚያቀርቡት ካሊፎርኔያ አሜሪካ በሚካሄደው አለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ውድድር ላይ እንደሆነም ተነግሯል፡፡

ከልጃገረዶች መካከል ስቴሲ ኦዊኖ እንዳለችው የሴቶች ግርዛት በአለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ችግር በመሆኑ ይህንን ለመቅረፍ ይፈልጋሉ፡፡

ልጃገረዶቹ የፈጠሩት መተግበሪያ ‹‹አይ ከት›› የሚል ስያሜ ያለው ሲሆን የጥቃቱ ተጋላጭ ሴቶች ድርጊቱ ከመፈፀሙና ከተፈፀመ በኋላ የተለያዮ እርዳታ እንዲያገኙ ያስችላል ተብሏል፡፡ 

ለአብነትም ልጃገረዶቹ ጥቃቱ ሲፈፀምባቸው ሰዎች እንዲታደጉዋቸው የድረሱልኝ ጥሪ ማቅረቢያ እና ሌሎች መረጃ ማስተላለፊያ መጥሪያዎች አሉት ነው የሚባለው፡፡

ምንጭ፦ሮይተርስ