የብሪክስ አባል አገራት የንግድ ጣልቃ ገብነትን ለመከላከል ተስማሙ

ሐምሌ 27፣2009

ቻይናን ጨምሮ ሌሎች የብሪክስ አባል አገራት ከሌሎች አገራት በታክስ፣ ቀረጥ የሚጣልባቸውን ችግሮች ለማቃለል በጋራ እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

የብራዚል፣ሩሲያ፣ ህንድ ቻይና እና ደቡብ አፍሪካ የንግድ ሚንስትሮች በሻንጋይ ባካሄዱት የሁለት ቀናት ስብሰባ የቻይና የንግድ ሚንስትር ዞንግ ሻን እንዳሉት አገራቱ የንግድና ኢቨስትመንት ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማምተዋል።

አገራቱ አስተማማኝና የዳበረ የንግድ ልውውጥ ለማድረግ እንደሚፈልጉ ተገልጿል።

ሚንስትሮቹ በቀጣይ የንግድና ኢንቨስትመንትን ክልከላ በመታገል በጋራ እንደሚቆሙም ተናግረዋል።

በአምስቱ አባል አገራት ትብብር የተዘጋጁ መመሪያዎችንም ማጽደቃቸውን ዘገባው ያስረዳል።

ምንጭ፤ ሮይተርስ