ፖል ካጋሜ የሩዋንዳን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አሸነፉ

ሐምሌ 29፤2009

በሩዋንዳው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ በሰፊ የድምጽ ልዩነት ማሸነፋቸውን የአገሪቱ  የምርጫ ኮሚሽን አስታውቋል።

እስከ አሁን ከተቆጠረው ሰማንያ ከመቶ ድምጽ ፕሬዝዳንቱ 98 ከመቶ ማግኘታቸው ተነግሯል። ፕሬዝዳንቱ  ባገኙት ውጤት መሠረት ለሶስተኛ ጊዜ ሩዋንዳን ይመራሉ፡፡

የፕሬዝዳንቱ ደጋፊዎች በአገሪቱ በ1994 ከተከሰተው አሰቃቂ የዘርጭፍጨፋ  በሃላ በአገሪቱ የተረጋጋ የኢኮኖሚ እድገት ማምጣቸውን ይናገራሉ።

በአብዛኛው ከአገር ውጭ የሚኖሩ ተቃዋሚዎቻቸው አገሪቱን የሚመሩት በማስፈራራት እንደሆነ ይገልጻሉ።

ከውጤቱ በኋላ ፕሬዝዳንቱ የአገሪቱን የኢኮኖሚ እድገት እንደሚያስቀጥሉ  ቃል ገብተዋል።

በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1994 ወደ  ስልጣን የመጡት የ59 አመቱ  ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ  አገራቸው ከዘር ዕልቂት አውጥተው ወደ ፈጣን ኢኮኖሚያዊ እድገት እንዳስገቧት  ይነገርላቸዋል።

ሩዋንዳ በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር  በ2015 ህገመንግስታዊ ማሻሻያ ከደረጋች በኃላ ነው ፕሬዝዳንቱ  ዳግም ተፎካካሪ ሆነው የቀረቡት።

ምንጭ:-ቢቢሲ