የታቀዱ ፕሮጀክቶችን ተከታትሎ ማሰራት በአውሮፓ ከተሞች ከፍተኛ ሙቀት ስጋትን ፈጥሯል

ሃምሌ 28፤2009

የአውሮፓ ከተሞች ባለፉት አስር አመታት ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ከፍተኛ የሙቀት መጠን አጋጥሟቸዋል፡፡

ሙቀቱም እስከ 44 ድግሪ ሴልሽየስ ይደርሳል ነው የተባለው፡፡

አንዳንድ ሀገራትም ሙቀቱ በህዝባቸው ላይ የጤና ቀውስን ሊያስከትል እንደሚችል እያስጠነቀቁ ይገኛሉ፡፡

በጣሊያን ሙቀቱ የሰደድ እሳትን የቀሰቀሰ ሲሆን የመጨረሻው የሙቀት አደጋ ማስጠንቀቂያ ላይ ለመድረስ እንዳስገደዳቸው ተነግሯል፡፡

ቱሪስቶችና ነዋሪዎችም ከሙቀቱ እራሳቸውን ለመከላከል ባገኙበት ቦታ በቀዝቃዛ ውሃ ውስጥ መነከርና መዋኘት ግድ ሆኖባቸዋል፡፡

ይህ ከፍተኛ ሙቀትም ለሚቀጥሉት አምስት ቀናት ሊቆይ እንደሚችል የአየር ትንበያ ባለሙያዎች አሳስበዋል፡፡

ምንጭ፡ ቢቢሲ