ኬንያውያን ፕሬዝዳንታቸውን ለመምረጥ ድምፅ መስጠት ጀምረዋል

ነሀሴ2 ፤2009

በኬንያ ዘንድሮ ለሚደረገው አጠቃላይ ምርጫ ዜጎች ዛሬ ከማለዳ ጀምሮ ድምፃቸውን መስጠት ጀምረዋል፡፡

ምርጫውን አስመልክቶ የወቅቱ የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ ለመምረጥ የተመዘገቡት 19 ሚሊዮን ዜጎቻቸው ፣ በነቂስ ወጥተው ድምፃቸውን እንዲሰጡና በሰላም ወደየቤታቸው እንዲገቡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በአገሪ ዙሪያ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ረጃጅም ሰልፎች ከወዲሁ መታየት ጀምረዋል፡፡

የምርጫውን ውጤት ተከትሎ ባለፉት ምርጫዎች የተከሰቱት ግጭቶች ዳግም እንዳይቀሰቀሱ ፍራቻው ቢኖርም በሁሉም ኬንያዊያን ዘንድ ያ ታሪክ እንዲደገም የሚፈልግ የለም ተብሏል፡፡

በፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬኒያታና በረጅም ጊዜ ተቀናቃኛቸው ራይላ ኦዲንጋ መካከል ማንኛቸው የዘንድሮውን ምርጫ ያሸንፋሉ የሚለው አሁንም ለግምት እጅግ አዳጋች ነው ተብሏል፡፡

የ55 ዓመቱ ከነፃነት መልስ የመጀመሪያው የኬኒያ ፕሬዝዳንት የበኩር ልጅ የሆኑት አሁሩ ኬንያታ ለሁለተኛና ለመጨረሻ ጊዜ በስልጣን ላይ ለመቆየት ነው በምርጫ የሚፋለሙት፡፡

የናሽናል ሱፐር አልያንስ መሪ የሆኑት ኦዲንጋ ምርጫውን ለማስከበር የተሰማሩት ከ150 ሺህ በላይ ወታደሮች መራጮችን ለማሸማቀቅ እንደሆነ ቢገልፁም ተቀናቃኛቸው ኬንያታ ጠንካራ ተፎካካሪያው መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በምርጫውም የበለጠው እንዲያሸንፍ ተመኝተዋል፡፡  

ምንጭ፡- ቢቢሲ