የተመድ ዋና ፀሐፊ የኬንያ ምርጫ ሰለማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ጥሪ አቀረቡ

ነሐሴ 02፣2009

የተመድ ዋና ፀሀፊ የኬንያ ምርጫ ሰለማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ጥሪ አቀረቡ፡፡

ዋና ፀሀፊው አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ኬንያ ዛሬ እያካሄደች  የሚገኘው ምርጫ  ተዓማኒ እንዲሆን ሁሉም ባለድሻዎች ተባብረው ሊሰሩ ይገባል ብለዋል፡፡

ዋና ፀሀፊው ሰብዓዊ መብትና መሰረታዊ ነፃነቶችን ማክበር ላይ ትኩረት ሊደረግ እንደሚገባም አመልክተዋል፡፡

ዋና ፀሐፊው የኬንያ ምርጫ ሂደትን በቅርበት ሲከታተሉት መቆየታቸውንና በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ ከሚመለከታቸው ባድርሻዎች ጋር ንግግር ሲያደርጉ መቆየታቸውን አስረድተዋል፡፡

በዛሬው የኬንያ ምርጫ 19 ሚሊያን ኬንያዊያን ይሰተፉበታል ተብሏል፡፡

ምንጭ፡‑ ሽንዋ