የደቡብ ሱዳን መንግስት የሀገሪቱን የአማፂያንን ዋና ማዘዣ ተቆጣጠረ

ነሀሴ2 ፤2009

የደቡብ ሱዳን መንግስት ጦር በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ የሚገኘውን የሀገሪቱ አማፂያን ጠንካራ ምሽግና ዋና ማዘዣ ፓጋክ የተባለችውን ከተማ ተቆጣጠረ፡፡

የሀገሪቱ ጦር ሰራዊት ‹‹ፓጋክ›› የተባለ የአማፂያኑን ዋና ጦር መምሪያና የአካባቢውን ከተማ እንደተቆጣጠረ የአማፂያኑ ቃል አቀባይ ዊሊያም ጋትጄዝ ዴንግ ተናግረዋል፡፡

አማፃያንኑ ማዘዣ ከተማቸውን በመንግስት ወታሮች ቢነጠቁም ፣በማፈግፈግ ዳግም ኃይላቸውን እያደራጁ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

የመንግስት ወታደሮች አማፂያኑ ያሉበት የጦር ሰፈር ከመድረሳቸው በፊት ታጣቂ ተቃዋሚ ሀይሎቹ ትተውት የሚሄዱትን የጦር መሳሪያ በመንግስት ሀይሎች ዳግም ጥቅም ላይ እንዳይውል ማቃጠላቸውን አመልክተዋል፡፡

የደቡብ ሱዳን ጦር ቃል አቀባይ ሉል ሩዓይ ኮዓንግ ለአሶሼትድ ፕሬስ ጦራቸው ከተማዋን ስለ መያዙ ግን ማረጋገጫ አልሰጡም፡፡

የሀገሪቱ መንግስት ጦርነቱን ለማርገብ በተናጠል የተኩስ አቁም ስምምነት ቢያደርግም ጦሩ ‹‹ማዉት‹‹ እና ‹‹ፓጋክ›› በተባሉ ቦታዎች ላይ ወታደራዊ ጥቃት በመፈፀም ላይ መሆኑን ተነግሯል፡፡

ምንጭ፦አሶሼትድ ፕሬስ