የደቡብ አፍሪካ ፓርላማ በፕሬዝዳንት ዙማ ላይ የመተማመኛ ድምጽ ሊሰጥ ነው

ነሐሴ 02፣2009

የደቡብ አፍሪካ ፓርላማ በፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ ላይ በሚስጢር የመተማመኛ ድምጽ  ሊሰጥ ነው፡፡

ፓርላማው ይህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ተቃዋሚ ፓርቲዎች  ፕሬዝዳንት ዙማን በሙስና ጠርጥረዋቸው  ጉዳዩን ለህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት ከወሰዱት በኋላ ነው ተብሏል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ከፓርላማው  በቂ የመተማመኛ ድምጽ የማያገኙ ከሆነ ከስልጣናቸው የሚወርዱ ይሆናል፡፡

በፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ መንግስት ውስጥ የተፈጠረው የፖለቲካ አለመረጋጋት በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ትልቅ ተጽዕኖ እየፈጠረ እንደሚገኝ ይነገራል፡፡

ገዢው ፓርቲ አፍሪካን ናሽናል ኮንግረስ በበኩሉ ይህ የመተማመኛ ድምጽ እንዲሰጥ የተወሰነው በፖለቲካ ሴራ እንደሆነና መንግስትን ለመጣል የታቀደ ነው ብሏል፡፡

ፕሬዝዳንት ዙማ ከዚህ ቀደምም በተደጋጋሚ የመተማማኛ ድምፅ  ሲሰጥባቸው ቆይቷል፡፡

የአፍሪካ ኮንግረስ ፓርቲ እስካሁን ደቡብ አፍሪካን  ከአፓርታይድ አገዛዝ ነፃ ካወጣ ወዲህ አገሪቱን በመምራት ላይ ያለ ቢሆንም፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በሙስናና ተያያዥ ጉዳዮች በአዳዲስ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አጣብቂኝ ውስጥ እየገባ ይገኛል፡፡

ምንጭ፡‑ ቢቢሲ