አልጀሪያ ከአፍሪካ ያለ ስጋት የሚኖርባት ሀገር መሆኗን አንድ ጥናት አመለከተ

ነሐሴ 02፣2009

ከአፍሪካ አልጀሪያው ህዝቦች  ያለ ፀጥታ ስጋት ችግር የሚኖርቧት አገር መሆኑን ጋሉፕ የተሰኘው የጥናት ተቋም አስታወቀ ፡፡

በሀገሪቱ ድምፅ ከሰጡ አልጀሪያውያን  መካከል 90 በመቶ የሚሆኑት  የሀገሪቱን ፀጥታ አድንቀዋል፡፡

በድምፅ መስጠቱ የተሳተፉ ዜጎች በሀገሪቱ ፖሊስ አባላት እና በምሽት ጉዞ ምንም ስጋት እንደሌለባቸው ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ሩዋንዳ 84 በመቶ ድምፅ በማግኘት ከአፍሪካ ሁለተኛዋ ያለስጋት የሚኖርባት ሀገር ተብላለች፡፡

ሞሮኮ፣ ግብፅ እና ኢትዮጵያ ከሶስተኛ እስከ 5ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡

በኢትዮጵያ 80 በመቶ የሚሆነው ድምፅ ሰጪ ያለ ስጋት እንደሞኖር መስክሯል፡፡

ጋቦን፣ ላይቤሪያ እና ደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ህዝቦች ደግሞ ስጋታቸው ከፍተኛ መሆኑን የሚያሳይ ድምፅ ሰጥተዋል፡፡

ጥናቱ በስልክ እና በአካል የተደረገ ሲሆን ከ15 ዓመት በላይ ዕድሜ ያላቸው ሰዎች ተሳትፈውበታል፡፡ 135 ሀገራት ደግሞ በጥናቱ መካተታቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡

ጋሉፕ የተሰኘው የአሜሪካ ተቋም እ.ኤ.አ በ1935 የተመሰረተና በአለም አቀፍ ደረጃ የህዝብ አስተያየት መለኪያዎችን በማዘጋጀት የሚታወቅ ነው፡፡