በኬንያ ምርጫ ፕሬዝዳንት አሁሩ ኬንያታ እየመሩ ነው

ነሐሴ 03፣2009

በኬንያ ምርጫ ፕሬዝዳንት አሁሩ ኬንያታ እየመሩ መሆኑን የአገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ትላንት በተካሄደው የኬንያ አጠቃላይ ምርጫ 80 በመቶ በተካሄደ የድምፅ ቆጠራ 55 በመቶውን ድምፅ ማግኘታቸው ተመልክቷል፡፡

ተፎካካሪያቸው  ራይላ ኦድንጋ ደግሞ 44 በመቶ ድምፅ አግንተዋል ተብሏል፡፡

ይሁንጂ የኬንያታ ተፎካካሪ ራይላ ኦድንጋ በከፊል የተገለፀውን የምርጫ ውጤት  በምርጫ  ኃላፊዎች ማረጋገጫ ያልቀረበበት በመሆኑ ተቀባይነት የለውም ብለዋል፡፡ይልቁኑ ውጤቱ በተፃፃራሪው በሰፊ ልዩነት የእኛ እንደሚመራ አመላካች መረጃዎች አሉን በሚል ተናግረዋል፡፡

የአገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ግን ህዝቡ ሙሉው ይፋዊ ውጤት እስኪገለፅ በትዕግስት እንዲጠብቅ አስገንዝበዋል፡፡

ብዙዎች በምርጫ ውጤት አለመግባባት የዛሬ 10 ዓመት ተከስቶ የነበረው የጎሳ ግጭት እንዳይቀሰቀስ ስጋት ገብቷቸዋል፡፡

በቅድመ ምርጫ ውጤቱ ገለፃ መሰረት ኬንያታ ሁለተኛውን የስልጣን ዘመናቸውን ያረጋጋጡ ይመስላል፡፡

የምርጫው ሙሉ ውጤት አሸናፊ ግን  ተጠቃሎ በሰባት ቀን ውስጥ ይገለፃል ተብሏል፡፡

ምንጭ፡‑ ቢቢሲ