ፌስ ቡክ ትክክለኛ መረጃ ያልያዙ መልዕክቶችን እንዳይጋሩ ሊያደርግ ነው

ነሀሴ 4 ፤2009

ፌስቡክ በድህረ ገጹ ላይ ትክክለኛ ያልሆኑ መረጃዎች ሲለቀቁ በሌሎች ተጠቃሚዎች እንዳይጋሩ ወይም ሼር እንዳይደረጉ መደበቅ ሊጀምር እንደሆነ አስተወቀ፡፡

ማህበራዊ ድረገፁ እንዲህ ማድረጌ ተጠቃሚው የሚያገኘው መረጃ ትክክለኛና የተጣራ እንዲሆን ያስችላል ብሏል᎓᎓

ፌስ ቡክ አደረኩት ባለው ጥናት ተጠቃሚዎች በየቀኑ የተለያዩ ሰዎች በፌስቡክ ገፃቸው የለጠፏቸውን መረጃዎች ሼር እያደረጉ ሰዎች በየቀኑ ማግኘት የሚገባቸውን መረጃ ይገድባል᎓᎓

በመሆኑም አንድ የፌስ ቡክ ተጠቃሚ በቀን መጋራት ወይም ሼር ማድረግ የሚችለውን ቁጥር ለመገደብ መገደዱን ነው ድርጅቱ ያስታወቀው፡፡

ምንጭ፡ ኢንዲፔንደንት ዩኬ