ፍርድ ቤቱ የከባድ ሙስና ወንጀል ተጠርጣሪዎቹን የዋስ መብት ጥያቄን ውድቅ አደረገ

ነሀሴ 4 ፤2009

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት በከባድ የሙሰና ወንጀል ተጠርጥረው ምርመራ እየተካሄደባቸው የሚገኙ ተጠርጣሪዎች ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ አደረገ፡፡

ችሎቱ ለተጨማሪ ምርመራ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የምርመራ ቡድን የጠየቀውን ተጨማሪ ጊዜ ፈቅዷል፡፡