ሴቶች ለአፍሪካ ሰላም ተሳታፊ ሊሆኑ እንደሚገባ አስታወቀ

ነሐሴ 05፣2009

አፍሪካውያን ሴቶች የአፍሪካን ሰላም  ለማረጋገጥ  ጠንካራ ተሳትፎ ሊኖራቸው እንደሚገባ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ፡፡

ለሰላም ሂደቱ ስኬት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የአፍሪካ ህብረት የአህጉሪቱን ሴቶች ማብቃት እንዳለባቸውም ተገልጿል፡፡

በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ጉብኝት ያደረጉት የተ.መ.ድ ምክትል ዋና ፀሃፊ አሚና ሞሃመድ እንዳሉት  በአፍሪካ ሰላም ዕጦት ምክንያት ሴቶች የፆታ ትንኮሳ፣ አስገዳጅ ጋብቻ እና ሌሎች ችግሮችን እያስተናገዱ ነው፡፡

በናይጀሪያ ደግሞ ሴቶችን ለአጥፍቶ ጠፊነት የመጠቀም ሂደት እየተበራከተ መሆኑንም ተብራርቷል፡፡

በመሆኑም መሰል ችግሮችን ለመቅረፍ ሀገራት ሴቶችን በሰላም እና ደህንነት እንዲሁም የልማት ስራዎች ማሳተፍ እንደሚገባ  ም/ዋና ፀሃፊዋ ገልጽዋል፡፡

የሴቶች ችግር በናይጀሪያ እና ዲ.ኮንጎ የገዘፈ እንደሆነ  ተገልጿል፡፡

ምንጭ፡ ሲጅቲኤን