በኬንያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ኡሁሩ ኬንያታ ማሸነፋቸው ተገለጸ

ነሀሴ 6 ፤2009

በኬንያ በተደረገ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በስልጣን ላይ ያሉት ኡሁሩ ኬንያታ ለሁለተኛ ጊዜ መመረጣቸውን የሀገሪቱ ምርጫ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

ኬንያታ አሸናፊ ሊሆኑ የቻሉት  ከተሰጠው አጠቃይ ድምጽ 54 ነጥብ 3 በመቶውን በማግኘት ሲሆን ተቀናቃኛቸው ሪያላ ኦዲንጋ ደግሞ 44 ነጥብ 7 በመቶውን ማግኘታቸው ተነግሯል፡፡

የኡሁሩ ኬንያታ ድል ከተገለጸ በኋላ ህዝቡ አንድነቱን እንዲያጠናክር ኬንያታ ጥሪ ማቅረባቸው ተገልጿል፡፡

ይሁን እንጂ ተቃሚዎች የምርጫ ውጤቱ ከመገለጹ በፊትም ቢሆን ውጤቱ ተጭበርብሯል በሚል እንደማይቀበሉት አስታውቀው ነበር፡፡

ውጤቱን ተከትሎ የተቃዋሚው ሪያላ ኦዲንጋ ደጋፊዎች በሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች ተቃውሞ እያስነሱ መሆናቸው ዘገባዎች ያመለክታሉ፡፡

የዩጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ እና የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜን ጨምሮ ሌሎች የአካባቢው ሀገራት መሪዎች ለኡሁሩ ኬንያታ የእንኳን ደስ አለህ መልዕክት መላካቸው ተነግሯል፡፡

ምንጭ፡ ቢቢሲ