የሆሳዕና ከተማ ነዋሪዎች የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ ማግኘት እንዳልቻሉ ገለጹ

ነሀሴ 6 ፤2009

በሆሣዕና ከተማ የመሬት ባለቤትነታቸው ቢታወቅም ለአስራ ሶስት አመታት ያክል የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ ጥያቄ ያልተመለሰላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች አሉ፡፡

ህገ-ወጥ ግንባታ ተካሂዶብናል የሚሉም ይገኙበታል፡፡

ነዋሪዎቹ ከሚኖሩበት ከአንዱ ቀበሌ በጥቂት ቀናት ውስጥ የይዞታ ማረጋገጫው እንደሚሰጥ ቢነገራቸውም አጠቃላይ ጉዳዩ የሚመለከተው የከተማው ማዘጋጀቤት ግን ምላሽ ሳይሰጥ ቀርቷል፡፡