በደቡብ ሱዳን ፓጋክ ከተማ ከፍተኛ ጦርነት መቀስቀሱ ተነገረ

ነሀሴ 6 ፤2009

ከኢትዮጵያ ድንበር በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘው የደቡብ ሱዳን ፓጋክ ከተማን ለመቆጣጠር በመንግስትና በአማፂያን ተፋላሚዎች መካከል ከፍተኛ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የመንግስት ጦር ሃይል ይህችን ከተማ ከጥቂት ቀናት በፊት ከአማጺያኑ ነጻ ያወጣ ሲሆን አሁን ደግሞ አማጺያኑ በተራቸው መልሰው ለመቆጣጠር ከመንግስት ጋር ውጊያቸውን እንደቀጠሉ ነው የተነገረው፡፡

በደቡብ ሱዳን የመንግስታቱ ድርጅት ሰላም አስከባሪ ልኡክ ለሮይተርስ በሰጡት መግለጫ በፓጋክ ከተማ ያለው ሁኔታ እጅጉን አሳሳቢ በመሆኑ ተፋላሚ ወገኖቹ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ከጥቂት ቀናት በፊት መንግስት የፓጋክ ከተማንና አካባውን ከአማጺያኑ ነጻ ማድተጉን ተከትሎ ከኢትዮጵያ የሚያስተሳስረውን የመንገድና ነዳጅ ማስተላለፊያ መስመርን ለመገንባት ማቀዱን መግለጹ የሚታወስ ነው፡፡

ምንጭ፡ ሮይተርስ