የኢትዮጵያ አየር መንገድ - የአፍሪካ አቪዬሽን ተምሳሌት

በአፍሪካ የግዙፉ ኢኮኖሚ ባለቤት ናት የምትባለው ናይጄሪያ ብሄራዊ አየር መንገድ ካጣች 14 አመታትን አስቆጥራለች፡፡

ሌሎች የአፍሪካ አየር መንገዶች ደግሞ እራሳቸውን በራሳቸው ገቢ መተዳደር እያቃታቸው ከመንግስት ድጎማን እያገኙ ቢሆንም አሁንም በርካቶቹ በገንዘብ ቀውስ ውስጥ ይገኛሉ፡፡

ከአፍሪካ ቀዳሚ አየር መንገድ በመባል በርካታ ጊዜ የሚመረጠው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአንጻሩ በራሱ በሚያመነጨው ገቢ እራሱን የሚያስተዳድር ሆኖ ትርፋማ አየር መንገድም ነው፡፡

በገንዘብ ቀውስ ውስጥ የወደቁትን የአፍሪካ አየር መንገዶችን የአክሲዮን ድርሻን ከመግዛት ባለፈ የአስተዳደራዊ ስራውንም ተረክቦ እየሰራላቸው ነው፡፡

ቢቢሲም ሌሎች የአፍሪካ አየር መንገዶች ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ምን ይማራሉ በሚል የሚከተለውን ዝግጅት አቀናብሯል፡፡