ለፖለቲካ ፓርቲዎች የፋይናንስ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ተወሰነ

ነሃሴ 6፤2009

ለፖለቲካ ፓርቲዎች የእለት ተእለት ሥራዎች ማስፈፀሚያ በመንግሥት የፋይናንስ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከስምምነት ላይ ደረሱ፡፡

የድጋፉ መስፈርትም ፓርቲዎቹ በምርጫ በሚያገኙት ድምፅና በሚያስመዘግቡት ዕጩ  እና በምክር ቤት ባላቸው መቀመጫ ብዛት እንዲሆን ተስማምተዋል፡፡