የታላቁ መሪ መለስ ዜናዊ ሕይወትን የሚዳስስ “የዘመን ክስተት” መፅሐፍ ተመርቀ

ነሃሴ 6፤2009

ታላቁ መሪ መለስ ዜናዊ በሕይወት ዘመናቸው የቀረጿቸው ፍኖተ ካርታዎች ለኢትዮጵያ መንገድ ጠቋሚ ሆነዋል ሲሉ በጠቅላይ ሚኒስቴር ፅሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ግንባታ አስተባባሪ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ተናገሩ፡፡

እነዚህ አስተሳሰቦችም ሊቀመጡና ለትውልድ ሊሸጋገሩ ይገባል ብለዋል፡፡

በታላቁ መሪ መለስ ዜናዊ የሕይወት ጉዞ ላይ ያተኮረ ""የዘመን ክስተት"" የተሰኘ መፅሐፍ ተመርቋል፡፡