የኢትዮጵያ የቱሪዝም ባለውለታ አቶ ኃብተስላሴ ታፈሰ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፀመ

ነሐሴ 7፣2009

የኢትዮጵያ የቱሪዝም ባለውለታ አቶ  ኃብተስላሴ  ታፈሰ የቀብር ስነ ስርዓት  ተፈፀመ፡፡

ዛሬ ነሐሴ 07፣2009 በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራልል ቤተክርስቲያን የተለያዩ የመንግስት ባለስልጣትና ወዳጅ ዘመዶቻቸው  በተገኙበት ነው የኢትዮጵያ የቱሪዝም አባት ተብለው የሚታወቁት አቶ ኃብተ ስላሴ ተፈሰ ቀብር ስነ ስርዓት የተከናወነው፡፡

በቀብሩ ስነ ስርዓት ላይ  የተገኙት የባህልና ቱሪዝም ሚንስትር ዶ/ር ሂሩት  ወልደማርያም አቶ ኃብተ ስላሴ  በኢትዮጵያ  የቱሪዝም ታሪክ  እድገት ላይ ታላቅ አስተዋፅኦ ማድረገቸውን ተናግረዋል፡፡

የቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስም አቶ ኃብተ ስላሴ ኢትዮጵያን በሌሎች አገራት በማስተዋወቅ መጠነ ሰፊ ስራ መስራታቸውን መስክረዋል፡፡

አቶ ኃብተ ስላሴ የ13 ወር ፀጋ  በሚል  መለያ  የኢትዮጵያን የቱሪዝም ሀብቶች  ለአመታት ሲያስተዋዉቁ ኖረዋል፡፡

ለዚህ አስተዋፅኦቸውም  ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳኝና ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር  ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

ባደረባቸው ህመም የህክምና ክትትል ሲደረግላቸው ቆይተው ነሐሴ 03፤2009 በ91 ዓመታቸው ያረፉትና ዛሬ ነሐሴ 07፣2009 ስርዓ ቀብራቸው የተፈፀመው  የአቶ ኃብተ ሥላሴ ታፈረ  የሶስት ወንድና አንድ ሴት ልጆች አባት ነበሩ፡፡

ሪፖርተር ፡‑ እዮብ ሞገስ