የህፃናት እንቅልፍ ማጣት ለስኳር በሽታ ያጋልጣል‑ ጥናት

ነሐሴ11፣2009

የእንቅልፍ ችግር ያለባቸው ህፃናት በተሻለ ከሚተኙ ህፃናት  የስኳር በሽታ ሊከሰትባቸው እንደሚችል እንግሊዛዊያን ተመራማሪዎች ገለፁ፡፡

በምሽት የተሻለ ሰዓት የሚተኙ ህፃናት የክብደት መቀነስ እና በደም ውስጥ የስኳር መስተካከል እንደሚታይባቸው ጥናቱ አመልክቷል ፡፡

ከአሁን ቀደም የስኳር በሽታ በህፃናት ላይ የተለመደ ባይሆንም አሁን ግን ብዙ ህፃናት የክብደት መጠናቸው ከፍተኛ በመሆኑ እና ብዙ ጣፋጭ ነግሮችን ስለሚመገቡ የስኳር ተጋላጭነታቸው ሰፍቷል ተብሏል፡፡

በተለይም በአዋቂዎች ዘንድ ብቻ ይከሰት የነበረው አይነት ሁለት የስኳር ህመም አሁን ላይ በህፃነናትም ላይ የተለመደ  ሁኗል ብሏል ጥናቱ፡፡

ጥናት ከተደረገባቸው 4ሺህ በላይ ህፃናት አማካኝ ትክክለኛው የመተኛ ሰዓታቸው ከ8 እስከ 12 ስዓት ሆኖ ተገኝቷል፡፡

ከ6 እስከ 12 ዓመት የሚገኙ ህፃናት መተኛት ያለባቸው ጤነኛ የእንቅልፍ ጊዜ  ከ9 እስከ 12 ሰዓት በቀን እንዲሆን የዘርፉ አጥኝዎች አስቀምጠዋል፡፡

በመሆኑም በጥናቱ መሰረት ከዚህ ሰዓት ያነሰ ጊዜ የሚተኙ ህፃናት የስኳር ህመም ስጋት ያለባቸው ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በተጨማሪም ህፃናቱ ከትክክለኛው ክብደት በላይ በመሆናቸው ለጤናቸው አስጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

በጥናቱ መስረት በቂ እንቅልፍ የማያገኙ ህፃናት እንዲርባቸው የሚገፋፋው ሆርሞንም ቀንሶ ታይቶባቸዋል፡፡ የመኝታ ሰዓታቸውን እና የመመገቢያ ሰዓታቸውን ማዘበራረቅም ለችግሩ መንስኤ እንደሚሆን አጥኝዎቹ አስቀምጠዋል፡፡

ወላጆች ለህጻናት መኝታ ብቻ ሳይሆን ከመኝታ በፊት ስሚደረግላቸው ንፅህናም መጨነቅ እንዳለባቸው ሮይተርስ በዘገባው አስፍሯል፡፡