ጠ/ሚ/ር ሃይለማርያም ደሳለኝ የኘሬዝዳንት ፓል ካጋሜ በዓለ ሲመት ላይ ለመገኘት ወደ ሩዋንዳ ሄዱ

ነሃሴ 12፤2009

ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ የሱዱን ጉብኝታቸውን አጠናቅቀው በኘሬዝዳንት ፓል ካጋሜ በዓለ ሲመት ላይ ለመገኘት ኪጋሊ ዛሬ ጠዋት ገብተዋል፡፡

የሩዋንዳው ኘሬዝዳንት ፓል ካጋሜ የበዓለ ሲመት ስነ ስርዓት ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝና ሌሎች የአፍሪካ መሪዎች በተገኙበት ዛሬ ይካሄደል፡፡

ፓል ካጋሜ ባለፈው ወር መጨረሻ በሀገሪቱ በተካሔደ ኘሬዝዳንታዊ ምርጫ ነበር ለ3ኛ ጊዜ የተመረጡት፡፡

የመራጩን ህዝብ ከፍተኛ ድምፅ በማግኘት ያሸነፉት ፓል ካጋሜ ለቀጣዮቹ 7 ዓመታት የሀገሪቱ ርዕሰ ብሔር በመሆን ያገለግላሉ፡፡

በሳሙኤል ከበደ