ቻይና በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎቿን ከድህነትን የማውጣቷን ጥረት አለም ባንክ አደነቀ

ነሐሴ 12፣2009

ቻይና በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎቿን  ከድህነትን የማውጣቷን ጥረት አለም ባንክ  አደነቀ፡፡

የአለም ባንክ ፕሬዚዳንት ጂም ዮንግ ኪም ቻይና በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ከድህነት ለማውጣት የወሰደችውን የፀረ- ድህነት እርምጃ የሚያስመሰግናት መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የፊታችን ታህሳስ የአለም ንግድ ድርጅትን ዓመታዊ ጉባኤ በምታስተናግደው ቦነስ አይረስ የተገኙት ፕሬዝዳንቱ፣ ከአርጀንቲናው ፕሬዝዳንት ማውሪሲዮ ማክሪ ጋር መክረዋል፡፡ ፕሬዚዳንት ጂም፣እ.ኤ.አ ከ1990ጀምሮ ከአለም ከድህነት ከወጡት 1.1 ቢሊዮን ሰዎች ውስጥ የቻይና ስኬት ውጤታማ የሆኑ ፖሊሲዎች መገለጫ ነው ብለዋል፡፡

ላለፉት 30 አመታት ቻይና በምጣኔ ሀብቷ ላይ ማሻሻያ እያደረገች በመምጣቷ ፣700 ሚሊዮን ሰዎችን ከድህነት ለማውጣት ችላለች፡፡ይህም በዚህ ጊዜ ውስጥ ከድህነት የወጣውን የህዝብ 70 በመቶ ድርሻ የሚይዝ ያደርገዋል፡፡

 በድህነት ቅነሳ ላይ የቻይና ማህበራዊ ሳይንስ አካዳሚና የሀገሪቱ ምክር ቤት በ2016 ያሳተሙት አመታዊ ሪፖርት እንዳመለከተው ቻይና በዚህ አሃዝ 70 በመቶ የሚሆነውን የአለምን ድህንት ቀንሳለች፡፡

በ2012 የቻይና የድህነት መጠን 10.2 በመቶ የነበረው በ2016 ወደ 4.5 በመቶ  ዝቅ  ብሏል፡፡

የቻይና መንግስት በ2020 በመላው ሀገሪቱ ድህነትን ለማስወገድ አቅዳ እየሰራች መሆኑ ተመልክቷል፡፡