ኡጋንዳ የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሀብቷን ለማልማት የቻይናን ኢንቨስትመንት እንደምትፈልግ አስታወቀች

ነሐሴ 15፣2009

ኡጋንዳ የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሀብቷን ለማልማት የቻይናን ኢንቨስትመንት ድጋፍ እንደምትፈልግ አስታወቀች፡፡

ኡጋንዳ የቻይናን የዘርፉን ኢንቨስትመንት ተሳትፎ የጠየቀችው እ.ኤ.አ በ2020 ለማሟላት  ያሰበችውን የኃይል አቅርቦት እውን ለማድረግ ነው፡፡

በቀጣዩ ዓመት የድፍድፍ ነዳጅን ለውጭ ገበያ ለማቅረብ የሚያገለግል የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር፣ማጣሪያና የነዳጅ ማከማቻ ጋን ግንባታ ለመጀመር አቅዳለች፡፡

አገሪቱ እነዚህን የዘርፉን የልማት ስራዎች ከሚቀጥሉት ሶስት አመታት ጀምሮ እውን ለማድረግ 15 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልጋት የኡጋንዳ ስታንቢክ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፓትሪክ ምዌሄር ገልፀዋል፡፡

ኡጋንዳ ይህን የገንዘብ ፍላጎቷን ለማሳካት ነው ቻይና በነዳጅና ተፈጥሮ ጋዝ ልማት ዘርፍ እንትሰማራ ጥያቄዋን ያቀረበችው፡፡

የቻይና ኩባንያዎችም ከኡጋንዳ ጋር ተባብሮ መስራት እንደሚፈልጉ ለሲጂቲኤን ተናግረዋል፡፡

ኡጋንዳ 6.5 ቢሊዮን በርሚል የሚገመት ነዳጅና 5 መቶ ጫማ  ኪዩብ የተፈጥሮ ጋዝ  እንዳላት መግለጿን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡

የቻይና ኩባንያዎች በኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎችና በአውራ ጎዳና ግንባታዎች ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡