የኳታር የንግድ ምክር ቤትና የኢትዮጵያ ልዑክ ተባብረው መስራት በሚችሉባቸው አማራጮች ላይ መከሩ

ነሐሴ 15፣2009

የኳታር የንግድ ምክር ቤትና የኢትዮጵያ ልዑክ ተባብረው መስራት በሚችሉባቸው አማራጮች ላይ በዶሃ  መከሩ፡፡

ከፌደራልመንግስትና ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የተውጣጣ ቡድንና በኳታር የኢትዮጵያ ኢምባሲ ከኳታሩ የንግድ ምክር ቤት ጋር በተለያዩ የኢንቨስትመንት ጉዳዮች ላይ ባለፈው ቅዳሜ በዶሃ ተወያይተዋል፡፡

የኢትዮጵያው ቡድን የኳታር ባለሀብቶች ወደ ኢትዮጵያ ቢመጡ አዋጭ የሆኑ እንደ ግብርና፣የማዕድን ማውጣት ስራ፣ግንባታና ሪል ስቴት ዘርፍ ሳቢ መሆናቸውን አስረድቷል፡፡

በውይይቱም የሁለቱ አገራት የንግድ ጉብኝት እንዲካሄድና የኢትዮ‑ ኳታር የቢዝነስ ፎረም እንዲመሰረት በማድረግ የሁለቱን አገራት ትብብር ለማሳደግ  ከስምምነት ተደርሷል፡፡

የኳታር የንግድ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ ሞሃመድ ቢን ጦዋር  ኢትዮጵያ ለኳታር ኢንቨስትመንት ተስፋ ፈንጣቂ ናት ብለዋል፡፡

የኳታር ባለሀብቶች በኢትዮጵያ አንዲሰማሩ ምክር ቤቱ ጥረት እንደሚያርግም ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ልዑክም ኳታራዊያን ወደ ኢትዮጵያ ቢመጡ በፈለጉት መስክ ቢሰማሩ አስፋጊው ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ገለፃ አድርጓል፡፡

ምንጭ፡‑ ገልፍ ታይምስ