የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ብራዚል ሳኦ ፖሎ የቀጥታ በረራ ሊጀምር ነው

ነሐሴ 23፣2009

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ሳኦ ፖሎ ብራዚል የቀጥታ በረራ አገልግሎት ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ፡፡

አየር መንገዱ ከአሁን ቀደም ወደ ሳኦ ፖሎ መብረር የቻለው ከቶጎ ሎሚ በመነሳት ነው፡፡

አየር መንገዱ አዲሱን በረራ መስከረም መባቻ ላይ ለመጀመር ማቀዱን አስታውቋል፡፡

አየር መንገዱ ረዥም በረራዎችን ለማድረግ ቦይንግ 787 አውሮፕላኖችን እንደሚጠቀም አስታውቋል፡፡

አየር መንግዱ ወደ ሳኦ ፖሎ እ.አ.አ 2013 መብረር መጀመሩ ይታወሳል፡፡

ሳኦ ፖሎ የብራዚል ትልቋ የንግድ ማዕክል ከተማ ነች፡፡

ምንጭ፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ