ለአፍሪካ የጤና ኢፍትሃዊ ተደራሽነት የፖለቲካዊ ቁርጠኝነት ማነስ መሆኑን የአለም ጤና ድርጅት ገለፀ

ነሐሴ 25፣2009

ለአፍሪካ የጤና ኢፍትሃዊ ተደራሽነት የፖለቲካዊ ቁርጠኝነት ማነስ መሆኑን የአለም ጤና ድርጅት ገለፀ፡፡

የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም በዝምባቡዌ እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ የጤና ሚንስትሮች ጉባኤ ላይ የአፍሪካ መሪዎች ለህዝቦቻቸው በቂ የጤና አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ ተጨባጭ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ጠይቀዋል፡፡

ድርጅቱ አጠናሁት ባለው ወቅታዊ መረጃ የአፍሪካ የጤና ገልግሎት ፍትሃዊ ተደራሽ ያለመሆኑ ምክንያት የፖለቲካዊ ቁርጠኝነት ማነስና አናሳ በጀት መመደብ መሆኑን አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡

ድርጅቱም የአፍሪካን ጤና ስርዓት ለማሻሻል መሪዎቹን የማንቀሳቀስ ኃላፊነት እንደሚወስድ አመልክቷል፡፡

ለዚህም የአፍሪካን የጤና መሰረተ ልማት እና የሰው ኃይል ማሟላት ፣የተሟላ የአገልግሎት መስጠት ፣የመረጃ ስርዓት፣የመድሃኒትና የመልካም አስተዳደር አቅርቦት ሊተኮርባቸው የሚገባቸው መሆኑ ዶ/ር ቴድርስ  አመልክተዋል፡፡

የአፍሪካ መሪዎች ህክምና ለማግኘት ወደ ውጪ እየተጓዙበት ባለበት ወቅት የዚህ ዓይነቱ መድርክ የታለመልትን ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት ማምጣት ያስችለዋል ወይ የሚለውን ጉዳይ አጠያያቂ እንዳደረገው ዶቼ ቬሌ ዘግቧል፡፡