አፍሪካዊያን ሰው አልባ አውሮፕላንን ለሰብአዊነትና ለንግድ አገልግሎት በስፋት ጥቅም ላይ እያዋሉት ነው

ነሐሴ 25፣2009

ሰው አልባ አውሮፕላንን ለሰብአዊነትና ለንግድ አገልግሎት ጥቅም ላይ በማዋል አፍሪካ ለቀሪው አለም ሞዴል እየሆነች  መምጧቷ ተገለፀ፡፡

አንድ የአሜሪካ የሮቦት ኩባንያ በአፍሪካ ለደም አቅሮቦት አገልግሎት የሚውል  ሰው አልባ አውሮፕላን  ይዞ በመግባቱ ግንባር ቀደም ያደርግዋል፡፡

መሰረቱን በሳን ፍራንሲስኮን ያረገው ዚፕ ለይን የተሰኘው የሮቦት ኩባንያ ለሩዋንዳ የደም ስርጭት ማእከላት በሙሉ የሰው አልባ  አውሮፕላን  የደም አቅርቦት  አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተገልጿል፡፡

ኩባንያው የደም አቅርቦት አገልግሎቱን ለመስጠት  በኢንተርኔት፣በጽሁፍ፣በስልክ ወይም በዋትስአፕ የሚደርሰውን ትእዛዘ መሰረት በማድረግ በሰው አልባ አውሮፕላን በ20 ደቂቃ ውስጥ ያደርሳል ተብሏል፡፡

የዚፕላይን ኩባንያ የአለም አቀፍ ተልእኮና እና የግንኙነቶች ኃላፊ ማጊ ጂም  ኩባንያው  የአገልግሎት ስርጭቱን በሌሎች አፍሪካ ሀገሮች ውስጥ ለማስፋፋት በውይይት ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ቢዝነስ ኢንሳይደር እንደዘገበው የአፍሪካ አገራት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በምዕራባዊያን የተሰሩ ፈጠራዎችን ቀድሞ ወደ ስራ በማስገባት ሂደት ቀዳሚ እየሆኑ መምጣታቸውን ዘግቧል፡፡

ሰው አልባ አውሮፕላንን ብዙ የአፍሪካ አገራት ለተለያዩ ተግባራት መጠቀም መጀመራቸውን መረጃው አመልክቷል፡፡

ከአፍሪካ ሞሮኮ  ፣ካሜሮን ፣ ማላዊ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሩዋንዳና ኬንያ ሰው አልባ አውሮፕላንን ለቱሪዝም፣ ለጤና አገልግሎትና ለኤሌክትሮኒክስ የንግድ ልውውጥ የሚጠቀሙ አገራት ናቸው፡፡

ምንጭ፡- ቢዝነስ ኢንሳይደር