የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የምርጫውን ውጤት ሰረዘ

ነሃሴ 26፤2009

በኬንያ የተካሄደውን ምርጫ ተከትሎ የፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ተጭበርብሯል ሲሉ የነበሩት ተሸናፊው ራይላ ኦዲንጋ ጉዳዩን የሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሲከታለው ቆይቷል፡፡

እናም ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ተጭበርብሯል በማለት ውጤቱን ሰርዞታል፡፡ በ60 ቀናትም ውስጥ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንዲካሄድ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡

ከምርጫው መጭርበር ጋር በተገናኘ የፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እጅ እንደሌለበት የገለጸው ፍ/ቤቱ የምርጫ ኮሚሽኑ ግን ምርጫውን በአግባቡ አልምራም በሏል፡፡

ባለፈው ወር ላይ በተካሄደው የኬንያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ኡሁሩ ኬንያታ 54.3  ከመቶ ድምጽ በማገኘት አሸናፊ መሆናቸውን የሀገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን ማስታወቁ አይረሳም፡፡

ይሁን እንጂ በወቅቱ ተሸናፊው ራይላ ኦዲንጋ ምርጫው ተጭበርብሯል የምርጫ ኮሚሽኑ የመረጃ መረብ ተጠልፏል በማለት የምርጫውን ውጤት አልቀበልም ማለታቻውን ተከትሎ ነበር ጉዳዩን ፍ/ቤቱ ሲመረምር የቆየው፡፡

የፍ/ቤቱን ውሳኔ የኡሁሩ ኬኒያታ ፓርቲ ቢቃወመውም የራይላ ኦዲንጋ ደጋፊዎች ግን ደስታቸውን አደባባይ በመውጣት እየገለጹ ነው፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ