ተመድ በሶመሊያ የአሚሶምን ተልዕኮ ጊዜ አራዘመ

ነሃሴ 26፤2009

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው  ምክር ቤት በሶማሊያ የሰላም አስከባሪ ሃይል የአሚሶምን የተልዕኮ ጊዜን በፈረንጆቹ እስከ ግንቦት 2018 ድረስ እንዲራዘም ወሰነ፡፡

ምክር ቤቱ የሰላም አስከባሪ ሃይሉን ቁጥር በፈረንጆቹ ጥቅምት 2018 ድረስ ወደ 20 ሺህ 620 እንቀነስ መወሰኑንም ገልጿል፡፡

በአሁኑ ሰዓትም አሚሶም 22 ሺህ 126 የሰላም አስከባሪ ሃይል አባላትን ያቀፈ ነው፡፡

ሶማሊያ ከአለም አቀፍ ለጋሾች በምታገኘው ድጋፍ በራሷ ጸጥታ ሃይል ሙሉ በሙሉ የሰላም ማስከበር ተግባሯን እንድትወጣ ለማድረግ የረጅም ጊዜ እቅድ ይዟል፡፡

አሚሶም አሁንም ለሶማሊያ ሰላምና መረጋጋት ዋንኛ ተዋናይ ሆኖ እንደሚቀጥልና ሀገሪቱ የጸጥታ ማስከበር ሂደቱን ከአሚሶም እንድትረከብም የሽግግር ጊዜውን ያግዛል ነው የተባለው፡፡

ምንጭ፡ ሺንዋ