ቻይና ለአፍሪካ ልማት ጠንካራ ድጋፍ እንደምትሰጥ አስታወቀች

ነሃሴ 29፤2009

ቻይና ከአፍሪካ ጋር ያላትን ግንኙነት የበለጠ በማጠናከር ለአፍሪካ ልማት የሚውል ጠንካራ ድጋፍ እንደምታደርግ የሀገሪቱ ፕሬዝዳብት ዢ ፒንግ አስታወቁ፡፡

ዢ ፒንግ ከደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ ጋር ከብሪክስ ጉባኤ ጎን ለጎን ባደረጉት ውይይት በባህር ኢኮኖሚኸ በኢንደስትሪያል ምርት፤ ባህል፤ ሳይንስና ቴክኖሎጂ፤ ጤና አጠባበቅና ቱሪዝም ላይ ጠንካራ የጋራ ትብብርን ማሳደግ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በአለም አቀፍ ዙሪያ በርካታ ጉዳዮች እየተቀያየሩ ቢመጡም  የአፍሪካን ተጠቃሚነትን በሚያጎላ መልኩ ያለውን ግንዑነት በማሳደግ ለአህጉሪቱ ልማት፤ ሰላምና መረጋጋት የበኩሏን ድጋፍ እንደምታደርግ ነው የገለጹት፡፡

እንደ ብሪክስ፤ ጂ20፤ ተመድና አፍሪካ ህብረት ባሉ አለም አቀፍና ቀጠናዊ ተቋማት መካከል ያለው ግንኙነትና ትብብርም የበለጠ እንዲጠናከር ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ በበኩላቸው በቻይናና በደቡብ አፍሪካ መካከል ያለው ግንኙነትና ትብብር እያደገ መምጣቱን አብራርተዋል፡፡

ምንጭ፡ ሲቲጂኤን አፍሪካ