በማሽቆልቆል ላይ የነበረው የናይጄሪያና የደቡብ አፍሪካ ኢኮኖሚ ማንሰራራት ጀመረ

ጳጉሜ 1፣2009

የኢኮኖሚ ቀውስ ያጋጠማቸው ናይጄሪያና ደቡብ አፍሪካ ኢኮኖሚያቸው ዳግም ማንሰራራት መጀመሩን ተነገረ፡፡

ለበርካታ ጊዜያት ሲያሽቆለቁል የከረመው የሁለቱ ሀገራት ኢኮኖሚ ያንሰራራው በያዝነው ዓመት ምጣኔ ሀብታዊ እድገት በማስመዝገባቸው እንደሆነ ተገልጿል፡፡ 

ይሁን እንጂ አሁን ላይ ናይጄሪያ ዓመታዊ አጠቃላይ ምርቷ ከአንድ ፐርሰንት በታች በመሆኑ ከኢኮኖሚ ድቀት ለመላቀቅ የምታደርገው ጥረት አዝጋሚ እንደሆነ ተመልክቷል፡፡

በአንፃሩ ደቡብ አፍሪካ ከ2 ነጥብ 5 በላይ ጤናማ የሚባል የኢኮኖሚ እድገት ብታስመዘግብም አሁንም ድረስ ከባድ የኢኮኖሚ ፈተናዎች እንደተጋረጡባት ተነግሯል፡፡

የሀገሪቱ የአሁኑ እድገትም የግብርናውን ምርታማነት በ33 በመቶ እንዲያድግ አስተዋጽኦ ሊያደርግ ይችላል ነው የተባለው፡፡

ሆኖም በደቡብ አፍሪካ 28 በመቶ የሚጠጋ ስራ አጥነት ችግር በመኖሩ ኢኮኖሚው ሳይረጋጋ ይቆያል ተብሏል፡፡

በናይጄሪያ ደግሞ የነዳጅ ዘርፎ የምርት አፈፃፀም ደካማ መሆኑን ተከትሎ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ እድገት ሊጎትት ይችላል ተብሎም ይጠበቃል፡፡

የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ከህዝብ ቁጥሩ እድገት እንዲመጣጠንም ዓመታዊ የሀገር ውስጥ ምርቱ በ3 በመቶ ማደግ እንዳለበት ተጠቁሟል፡፡

ምንጭ፦ቢቢሲ