የሞጆ ደረቅ ወደብ እና የጅቡቲ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች በሙስና ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ

ጳጉሜ 02፣2009

ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክ አገልግሎት ድርጅት በሙስና የተጠረጠሩ ተጨማሪ ሁለት ኃላፊዎች  በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

የድርጅቱ አምስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በዚህ ሳምንት በሙስና ተጠርጥረው ባለፈው በቁጥጥር ስር ውለው ነበር፡፡

ከአምስቱ የስራ ኃላፊዎች በተጨማሪ  በቁጥጥር ስር የዋሉት የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክ አገልግሎት ድርጅት  የስራ ኃላፊዎቹ የሞጆ ደረቅ ወደብ  ስራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ ታዬ ጫላ እና የጅቡቲ ቅርንጫፍ ስራ  አስኪያጅ የነበሩት አቶ እውነቱ ታዬ ናቸው፡፡

ተጠርጣሪቹ ከጅቡቲ ተይዘው በቁጥጥር ስር መዋላቸው  ለማወቅ ተችሏል፡፡