አሜሪካ የሰሜን ኮሪያውን ፕሬዝዳንት ንብረት እንዲታገድ ሀሳብ አቀረበች

ጳጉሜ 2፣2009

አሜሪካ በሰሜን ኮሪያው የፕሬዚዳንት ኪም ጆንግ ዩን የግል  ንብረቶችን ጨምሮ በአገሪቱ ላይ አዲስ  ማዕቀብ እንዲጣል  ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የውሳኔ ሃሳብ  አቀረበች፡፡

አሜሪካ ያቀረበችው አዲስ ማዕቀብ የሰሜን ኮሪያ  የነዳጅ ምርት አቅርቦት፣ ወደ ውጪ በምትልካቸው የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ውጤቶችን ጨምሮ በፕሬዝዳንቱ  የግል ንብረቶች ላይ እገዳ የሚጥል ነው፡፡

የውሳኔ ሃሳቡ ለፀጥታው ምክር ቤት አባላት የተሰራጨው ሰሜን ኮሪያ ስድስት የኒዩክሌር ሙከራ እና ተደጋጋሚ  ሚሳይሎችን ከተኮሰች በኃላ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ምንጭ- ቢቢሲ