ሜክሲኮ በከባድ ርእደ መሬት ተመታች

ጳጉሜ 3፣2009

ሜክሲኮ በከባድ ርእደ መሬት መመታቱዋን የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ኢንሪኬ ፔና ገለፁ፡፡

በአደጋውም በትንሹ የ27 ሰዎች ህይወት ማለፉን ተነግሯል፡፡

በሬክተር ስኬል 8 ነጥብ 2 የተመዘገበው ይህ የመሬት መንቀጥቀት በፓስፊክ ውቅያኖስ ተከስቶ ደቡባዊ የሜክሲኮ ወደብን አናውጧል ተብሏል፡፡

የርእደ መሬቱን አደጋ ተከትሎም በቀጠናው የሚገኙ አገራት በተለይም ሜክሲኮ ላይ ሶስት ሜትር ከፍታ ባለው የውቂያኖስ ማዕበል/ሱናሚ/ ሊመቱ እንደሚችሉ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል፡፡

‹‹ኦክሳካ›› እና ‹‹ቺፓስ›› የተባሉ የአገሪቱ ግዛቶች በርእደ መሬቱ አደጋ ክፉኛ መመታታቸውንም ተጠቁሟል፡፡

በእነዚህም አካባቢዎች የፈረሱ ህንፃዎችና የመሰረተ ልማት አውታሮች እንደሚስተዋሉም ተጠቅሷል፡፡

የመሬት መንቀጥቀጡ በባለፉት 100 ዓመታት በሜክሲኮ ታሪክ ከባዱ እንደሆነ የገለፁት ፕሬዝዳንት ኢንሪኬ ፔና በአደጋው የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል ተናግረዋል፡፡ 

ምንጭ፦ቢቢሲ