ደቡብ ሱዳን ምርጫ ለማካሄድ መወሰኗን ተከትሎ ጥንቃቄ እንዲደረግ ተመድ አሳሰበ

ጳጉሜ 3፣2009

ደቡብ ሱዳን በሚቀጥለው አመት ምርጫ ለማካሄድ እቅድ መያዟን ተከትሎ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአገሪቱ ያለው የእርስ በርስ ጦርነት እንዳይባባስ ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስቧል᎓᎓

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ የአፍሪካ ህብረት ልዩ ልኡክ ሃይሌ መንቄሪዮስ የመንግስታቱ ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤትና የአፍሪካ ህብረት የሰላምና የደህንነት ምክር ቤት ባካሄዱት የጋራ ስብሰባ እንደገለጹት ደቡብ ሱዳን በሚቀጥለው አመት የምታደርገውን ምርጫ በትኩረት እየተከታተሉት ነው᎓᎓

የደቡብ ሱዳን ምርጫ መከናወን ያለበት በተረጋጋ አካባቢ ህዝቡ በርሃብና በረብሻ ሳይፈናቀል የፖለቲካ አመለካከታቸውን ያለማንም ጣልቃ ገብነት መግለጽ ሲችሉ ብቻ መሆኑን የልኡካን ቡድኑ አስታውቋል᎓᎓

የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ደቡብ ሱዳን ነጻ ከወጣች ለመጀመሪያ ጊዜ በርሳቸው መሪነት ምርጫ እንዲካሄድ ፍላጎት አላቸው᎓᎓

የእአአ በ2015 የተቀደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በ2013 በጀመረው የእርስ በርስ ጦርነት ምክንያት መዘግየቱ ይታወሳል᎓᎓

በግጭቱ ምክንያት በ10 ሺዎች የሚገመቱ ሰዎች ሞተዋል፣ 2ሚሊዮን ዜጎች ደግሞ አገራቸው ጥለው ተሰደዋል።

6 ሚሊዮን ወይም የአገሪቱ ግማሽ የሚሆኑ ዜጎች ለምግብ ዕጥረት መጋለጣቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገልጿል᎓᎓

ምንጭ:-አሶሼትድ ፕረስ