የኢትዮጵያውያን አንድነት የሁሉ ነገር መሠረት ነው- አቶ አባዱላ ገመዳ

ጳጉሜ 4፤2009

የኢትዮጵያውያን አንድነት የሁሉ ነገር መሠረት በመሆኑ ሁሉም ሊጠብቀው እንደሚገባ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አባዱላ ገመዳ አሳሰቡ፡፡

አፈ ጉባኤው በዛሬው ቀን እየተከበረ ያለው የአንድነት ቀንም በጽኑ መሠረት ላይ የተገነባው የኢትዮጵያውያንን አንድነት ይበልጥ ጠብቀን ለማቆየት ቃላችንን የምናድስበት ነው ብለዋል፡፡

በልዩነታችን ውስጥ ያለው አንድነታችን ድህነትን ለማስወገድ በጋራም ለመበልፀግ መሠረት ነው ብለዋል፡፡

አለማችንን አስተማማኝ ካደረጉት ነገሮች ውስጥ በልዩነታችን ውስጥ ያለው አንድነታችን በመሆኑ ሁሉም ህብረተሰብ ሊጠብቀው ይገባል ነው ያሉት፡፡

የኢትዮጵያውያንን አንድነት የሚሸረሽር የትኛውም ሀይል በጋራ መታገል እንደሚገባም አፈጉባኤ አባዱላ ገመዳ ገልፀዋል፡፡