ተመድ በሰሜን ኮሪያ ላይ አዲስ ማዕቀብ ጣለ

መስከረም 02፣2010

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰሜን ኮሪያ የኒውክለር ሙከራ ማካሄዷን ተከትሎ አዲስ ማዕቀብ ጣለባት፡፡

ሰሜን ኮሪያ ከአሜሪካ ጋር በገባችው እልህ ጭምር ላለፉት ስድስት ተከታታይ ጊዚያት የኒውክለር ጦር መሳሪያ ሙከራ ማድርጓን ተከትሎ  በኮሪያ ልሳነ ምድር ውጥረት ውስጥ ነግሶ ነበር፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሰሜን ኮሪያ ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ጥያቄ በቀረበለት የውሳኔ ሀሳብ መሰረት በትላንትናው ዕለት ነዳጅ በከፊል የማስገባት እገዳ እና የጨርቃጨርቅ ምርቷን ለውጭ ገበያ ማቅረብ እንዳትችል የሚያደርግና ሌሎች ክልከላዎችን ጨምሮ ማዕቀብ  ጥሎባታል፡፡

ይህም አገሪቱ ለጦር መሳያ መርሃ ግብሩ ማጎልበቻ የምትጠቀምበትን ነዳጅና ከወጪ ምርት የምታገኘውን ገቢዋን ለማራቆት ነው ተብሏል፡፡

አሜሪካ ቀደም ብሎ ሰሜን ኮሪያ ላይ  ሙሉ ለሙሉ ነዳጅ ማስገባት እንዳትችል ማድረግን ጨምሮ ከበድ ያለ ማዕቀብ እንዲጣልባት ጠይቃ ነበር፡፡

የሰሜን ኮሪያ ወዳጆች ናቸው የሚባሉት ሩሲያና ቻይና የሚጣለው ማዕቀብ ቀለል እንዲል የጠየቁት ሀሳብ ምላሽ በማግኘቱ  ትላንት የድርጅቱ የፀጥታው ምክር ቤት የጣለው ማዕቀብ በሙሉ ድምፅ እንዲፀድቅ አስችሎታል፡፡

ሰሜን ኮሪያም የተጣለባት ማዕቀብ ክፉኛ አስቆጥቷል ተብሏል፡፡

ሰሜን ኮሪያ በተጣለባት ማዕቀብ ከ1.2 ቢሊዮን ዶላር በላይ ያሳጣታል፡፡መሪው ኪም ጆንግ ኡን ወደ ውጭ አገራት እንዳይጓዙ እገዳ ይጣል የሚለውና በውጭ የሚኖሩ ዜጎቿ ሙሉ ለሙሉ የስራ እገዳ ይጣልባቸው የሚለው ሀሳብ በከፊል ተቀባይነት አላገኘም፡፡

ምንጭ፡‑ ቢቢሲ