ዚምባብዌ የፀሀይ ሀይል አቅርቦትን ለግብርና ምርታማነትና ለገጠር ሆስፒታሎች ስራ ላይ አውላለች

መስከረም 02፣2010

ዚምባቢዌ የፀሀይ ሀይልን በመጠቀም የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግና የገጠር አካባቢ ሆስፒታሎችን አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ እየተጠቀመች ነው።

በአብዛኛው የዚምባብዌ ገጠር አካባቢዎች  አብዛኛው ዝናብን መሰረት ያደረጉ የግብርና ስራዎች ባለፉት ሁለት አስርት አመታት  በተከሰተ የአየር ለውጥ ምክንያት ለምርት ማሽቆልቆል ተዳርገዋል፤  አብዛኛው የኤሌክትሪክ ሀይል  ማመንጫ ግድቦች ሃይል ማምረት  እንዲያቋርጡ እስከማድረግ አስገድዷል።

የዚምባብዌዋ ማሻባ ክልል ግን ሞቃታማና ደረቅ አካባቢዋን ወደ አረንጓዴ ለመቀየር  ከአውሮፓውያኑ  2015 ጀምሮ የጸሀይ ሀይል ማመንጫዎችን ተክላ እየተጠቀመች ነው።

በአካባቢው የመስኖ ስራዎችን በማከናወን የእርሻ ሰብሎችን ምርታማነትን ለማሳደግና ለኢኮኖሚ እድገትን የሚያግዝ አንድ መቶ ኪሎዋት የሚጠጋ ሀይል የሚያመነጩ  አራት መቶ  ፓነሎች ጥቅም ላይ እየሰጡ ነው።

በዚህም ትምህርት ቤቶች የበለጠ ምርታማ እንዲሆኑና የህክምና አቅርቦቶች አስተማማኝ እንዲሁን እያደረገ መሆኑን የአካባቢው መሪዎች ተናግረዋል።

የሀይል ማመንጫው 32 ሄክታር በመሬት በመስኖ የማልማት አቅም አለው ።

ይህን ፕሮጀክት እውን የሆነው ከአውሮፓ ህብረትና ከአለም አቀፍ ነዳጅ አምራችና ላኪ ድርጅት በተገኘ የ3.2 ሚሊዮን ዶላር በጀት ነው፡፡

ምንጭ፡‑ ሮይተርስ