ቡና አብቃይ ገበሬዎች በአየር ንብረት ለውጥ ሊጎዱ እንደሚችሉ አንድ ጥናት አመለከተ

መስከረም 02፣2010

በአም ሙቀት መጨመር ምክንያት ቡና ወዳጆች የሚወዱትን ካፊን ከጥቂት አመታት በኋላ ከቡና ማግኘት እንደሚቸገሩ አንድ ጥናት አመለከተ ᎓᎓

በአለም ሙቀት መጨመር ምክንያት ከአለማችን ቡና አምራች አገሮች ከፍተኛውን ምርት በማምረት የሚታወቁ የላቲን አሜሪካ አገሮች በአውሮፓውያኑ 2050 88 ከመቶ ምርታቸውን እንደሚቀንስ ሳይንቲስቶች  አስታውቀዋል።

በእስያና በአፍሪካ የሚገኙ ቡና አምራቸ አገሮች በተመሳሳይ ሁኔታ እንደሚጎዱ ነው ጥናቱ ያመለከተው᎓᎓

ሳይንቲስቶቹ ይህንን ለመተንበይ ያበቃቸው የአለም ሙቀት መጨመር በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2050 በ2.6 ዲግሪ ሴሊሸስ ሊጨምር እንደሚችል በመተንበዩ ነው።

በአውሮፓውያኑ 2015 በፓሪስ ከተማ በተካሄደው የአየር ንብረት ለውጥ ውይይት 200  የሚሆኑ  ሃገራት የአለም ሙቀት ከ 2 ዲግሪ ሰሊሸስ በታች እንዲሆን ቢስማሙም ይህ ግን ለመሳካቱ አንዳንዶቹ በጥርጣሬ ነው የተመለከቱት᎓᎓

ቡና ከ60 በላይ በሆኑ ሃገራት 2.5 ሚሊዮን በሚሆኑ ገበሬዎች የሚመረት ሲሆን በምርት ሂደቱ ከ100 ሚሊዮን ህዝብ በላይ ቢሳተፉም አብዛኞቹም ደሃና በገጠር የሚኖሩ ሰዎቸ መሆናቸውን በቬርሞት ዩኒቨርስቲ የአካባቢ ባለሙያ ቴይለር ሪኬትስ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል እንደ ሜክሲኮ፣ ጓቲማላ፣ ኮሎምቢያና ኮስታሪካ የመሰሉ አገራት መሬት ለቡና ምርቱ  ምቹ  ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል ሳይንትስቶቹ።

ምንጭ:-ሮይተርስ