የልማትና የመልካም አስተዳዳር ስራዎችን አጠናክሮ እንደሚያስቀጥል የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ገለጸ

መስከረም 02፣2010

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት አመታት የተመዘገቡ የልማትና የመልካም አስተዳዳር ስራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል እንደሚሰራ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ አሻድሊ ሀሰን ገለፁ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ አዲሱን አመት በማስመልከት ከ1ዐዐ በላይ ለሚሆኑ የህግ ታራሚዎች ምህረት መደረጉንም አታውቀዋል፡፡

ከክልሉ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ለደረሰን ዘገባ ሙባረክ ሙሃመድ፡፡