ኢትዮጵያ ከንብ ማነብ ዘርፉ የምታገኝው ገቢ ዝቅተኛ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ

መስከረም 3፣2010

በኢትዮጵያ በንብ ማነብ ስራ ላይ ባለው ዝቅተኛ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም እና ሌሎች ምክንያቶች ሳቢያ ሀገሪቱ ከዘርፉ የምታገኝው ገቢ ዝቅተኛ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ኢትዮጵያ በዓመት 5ዐዐሺ ቶን ማር የማምረት አቅም ያላት ቢሆንም በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት 444ቶን ማር በማምረትና ለውጭ ገበያ በማቅረብ አንድ ነጥብ አራት ሚሊየን ዶላር ብቻ ነው ያገኝችው፡፡

ይህም ካላት አቅም 1ዐ በመቶ በታች የሚሆንነው ብለዋል የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር መብራሃቱ መለስ፡፡

እናም የማር ምርት ብዛትን እና ጥራትን ለማሳደግ በዘርፉ ለተሰማሩት ወጣቶችና ባለሀብቶች ድጋፍ በማድረግ ቴክኖሎጂዎች ተጠቅመው እና እሴት ጨምረው ለገበያ እንዲያቀርቡ በ2ዐ1ዐ በትኩረት ለመስራት መዘጋጀቱን ነው የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለኢዜአ የገለፀው፡፡